Ministry of Education Ethiopia
@ethio_moe
This is Ministry of Education's Official Telegram Channel. For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe
Open in Telegram
Channel
Subscribers
149.9K
Current member count
Type
Channel
Telegram channel
Global Rank
#37
Directory ranking
Live Channel Feed
View on Telegram
የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ማጠናከር የገጠሩንናና የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የመረጃና የትምህርት ተደራሽነት እንደሚያሳድግ ተገለጸ፤
---------------------- // -------------------
(ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ተገቢውን ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡበት ሁኔታ በመዲናችን አዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔትና የህትመት ሚዲያዎች ተደራሽ ባልሆኑባቸው እንዲሁም የቋንቋ ውስንነት ባላቸው የገጠርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ዋና የመረጃ ምንጭ በመሆናቸው፣ አቅማቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ዩኔስኮ ባዘጋጀው መድርክ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ከማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር ለሚተገብሩት ፕሮጀክት ውጤታማነት ከጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ለወጣቶች የሚሰጡትን ትምህርታዊ አገልግሎት ጥራት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሐፊ አቶ ዓለሙ ጌታሁን፤ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ለገጠሩና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ወሳኝ ፋይዳ አብራርተዋል።
አክለውም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ወላጆች፣ መምህራን፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ መሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሬዲዮ ጣቢያዎቹ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18XdzZ9wRh/የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን ማጠናከር የገጠሩንናና የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የመረጃና የትምህርት ተደራሽነት እንደሚያሳድግ ተገለጸ፤
---------------------- // -------------------
(ጥቅምት 03/2019 ዓ.ም) የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ተገቢውን ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡበት ሁኔታ በመዲናችን አዲስ አበባ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱም የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች የቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔትና የህትመት ሚዲያዎች ተደራሽ ባልሆኑባቸው እንዲሁም የቋንቋ ውስንነት ባላቸው የገጠርና አርብቶ አደር አካባቢዎች ዋና የመረጃ ምንጭ በመሆናቸው፣ አቅማቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ዩኔስኮ ባዘጋጀው መድርክ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ከማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ጋር ለሚተገብሩት ፕሮጀክት ውጤታማነት ከጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ለወጣቶች የሚሰጡትን ትምህርታዊ አገልግሎት ጥራት ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የብሔራዊ ዩኔስኮ ዋና ጸሐፊ አቶ ዓለሙ ጌታሁን፤ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ለገጠሩና ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ያላቸውን ወሳኝ ፋይዳ አብራርተዋል።
አክለውም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ወላጆች፣ መምህራን፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ መሪዎች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የአካባቢው ባለሥልጣናት በንቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ የሬዲዮ ጣቢያዎቹ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/18XdzZ9wRh/
Oct 13, 01:46 PM
11.2K

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩየትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 19ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከበሩ
Oct 12, 08:38 AM
22.4K

Oct 10, 11:41 AM
31.6K

Oct 10, 11:38 AM
29.4K

📢 ማስታወቂያ
📌 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡
በጊዜያዊ ምደባ ሂደቱ ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጣራት ሥራ ተጠናቆ ምላሽ የተሰጠ በመሆኑ፣ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የምደባ መረጃችሁ በቀጥታ ለየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚላክ ሲሆን፣ ተቋማቱ በሚያወጡት የጥሪ መርሃ-ግብር መሠረት በጊዜያዊነት ወደተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመሄድ ትምህርታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።
እንዲሁም የተስትካከለ ምደባ ሊኖር ስለሚችል ከመሄዳቹህ በፊት በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባት https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ እንድታረጋግጡ ይሁን
📌 አዲስ ተማሪዎች፡
የምደባ ቦታችሁን https://student.ethernet.edu.et/view-placement/ በሚለው ማስፈንጠሪያ በመግባት ማረጋገጥ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፦ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ስለሆነ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታችሁን መቀጠል የምትፈልጉ ተማሪዎች(በጊዜያዊነት የተመደባችሁትን ጨምሮ) ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚያወጡትን የጥሪ ማስታወቂያ በመከታተል ትምህርታችሁን በነበራቹሁበት መቀጠል እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
ትምህርት ሚኒስቴር
Oct 10, 04:27 AM
36.7K
Safety & Compliance Disclaimer
TelePilot Pro is not affiliated with Telegram. Listings are based on publicly available community information. We index public groups, channels, and bots only. No private user data, phone numbers, or locked session files are stored or displayed.
TelePilot Pro Automation
Scale Your Telegram Community Faster
Join thousands of marketers using TelePilot Pro to bulk message, scrape targeted members, and manage groups on autopilot. Outperform competitors with our 40+ professional automation tools.