TelePilot Pro
Yeka Education

Yeka Education

@dam76

Education is the passport of the future!!

Subscribers
44.7K
Current member count
Type
Channel
Telegram channel
Global Rank
#79
Directory ranking

Live Channel Feed

View on Telegram
🤩🤩ዉጤታማ የአጠናን ዘዴዎች ✅ለነገ ዝግጁ ሁኑ!!!...ሁልጊዜም ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ነገ ለምትሰሩት ዕቅድ በማዉጣት ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል! ✅በየቀኑ የተማራችሁትን ማንበብ  መከለስና ከስር ከስር ማጥናት! ✅የተመጠነ የንባብ ጊዜ መመደብ ፤መሠላቸት ሳይኖር በተነቃቃ መንፈስ ዉጤታማ ጥናት ለማካሄድ በቂ ሰዓት መጠቀም! ✅የምናጠናቸዉን የት/ት አይነቶች በጊዜ መከፋፈልና ቅደም ተከተል ማስያዝ! በጥናት ወቅት ከጨዋታና ማህበራዊ ሚዲያ ራስን ማራቅ! ✅ምቹ እና ትኩረት ለማድረግ የሚረዳ የጥናት ቦታ መምረጥ እንዲሁም ለጥናት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በቅድሚያ ማዘጋጀት! ✅ማስታወሻ በአጭር በአጭሩ መያዝ እና አይገባኝም ከሚል አስተሳሰብ መዉጣት! ✅በት/ቤት የጥናት ቡድን መፍጠር ፤ከትምህርት አቻ ጓደኞቻችን ጋር እዉቀትና ልምዶችን መጋራት! ✅በየጊዜው የሚሰጡ የክፍል ፈተና ጥያቄዎችን ደጋግሞ መስራትና ከስህተት መማር! ✅ስናነብ ግልጽ ያልሆኑልን ነጥቦች ካሉ ማስታወሻ ይዞ ከመምህራን ጋር መወያየት! ወይም ደግሞ ከገባቸው ልጆች መረዳት ✅መፅሐፍትን በpdf የማንበብ ልምዳቺን ይሁን! በፈለግንበተ ቦታና ሰዓት ማንበብ ያስችለናል፣ 🖍የፈተና ጊዜ እየመጣ ነው በእቅድ እናጥና! 💓 መልካም  የጥናትና የት/ት ጊዜ!. 🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤 ቻናላችን ⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76
Nov 25, 03:29 PM
10.7K
🔤Questions about laboratory tools 1. Which tool is used for measuring precise volumes of liquids in the laboratory?    a) Graduated cylinder    b) Beaker    c) Test tube    d) Flask 2. What instrument is primarily used for heating substances in the laboratory?    a) Thermometer    b) Pipette    c) Bunsen burner    d) Stirring rod 3. Which of the following is used for transferring small amounts of liquid?    a) Beaker    b) Graduated cylinder    c) Pipette    d) Erlenmeyer flask 4. What is the purpose of a burette in the laboratory?    a) Measuring precise volumes of liquids    b) Heating substances    c) Dispensing small amounts of liquid    d) Mixing solutions 5. Which tool is used to hold and mix small quantities of liquids?    a) Beaker    b) Test tube    c) Erlenmeyer flask    d) Stirring rod 6. Which instrument is used to measure temperature in the laboratory?    a) Thermometer    b) Bunsen burner    c) Balance    d) Pipette 7. What is the primary function of a microscope in the laboratory?    a) Measuring mass    b) Observing small objects or organisms    c) Heating substances    d) Mixing solutions 8. Which tool is used for accurate weighing of substances in the laboratory?    a) Graduated cylinder    b) Beaker    c) Balance    d) Flask 9. What tool is commonly used to hold and transport small amounts of solid substances?    a) Beaker    b) Test tube    c) Petri dish    d) Erlenmeyer flask 10. Which tool is used to measure the pH of a solution in the laboratory?     a) Bunsen burner     b) pH meter     c) Graduated cylinder     d) Pipette 11. What is the primary use of a centrifuge in the laboratory?     a) Heating substances     b) Measuring volume     c) Separating components of a mixture based on density     d) Mixing solutions 12. Which tool is used for mixing small amounts of liquids or for grinding solids into fine powders?     a) Beaker     b) Erlenmeyer flask     c) Mortar and pestle     d) Pipette 13. What is the primary function of a spectrophotometer in the laboratory?     a) Measuring temperature     b) Observing microscopic objects     c) Analyzing the concentration of substances in a solution     d) Dispensing precise volumes of liquids 14. Which tool is used to measure the electrical conductivity of a solution in the laboratory?     a) pH meter     b) Bunsen burner     c) Conductivity meter     d) Graduated cylinder 15. What is the primary function of a petri dish in the laboratory?     a) Measuring volume     b) Observing microscopic objects     c) Growing microorganisms     d) Mixing solutions 16. Which tool is used for accurate dispensing of small volumes of liquid?     a) Beaker     b) Graduated cylinder     c) Pipette     d) Erlenmeyer flask 17. What is the primary function of a hot plate in the laboratory?     a) Measuring temperature     b) Heating substances     c) Observing microscopic objects     d) Dispensing precise volumes of liquids 18. Which tool is used for holding and organizing multiple test tubes during experiments?     a) Beaker     b) Test tube rack     c) Graduated cylinder     d) Erlenmeyer flask 19. What is the primary function of a stopwatch in the laboratory?     a) Measuring temperature     b) Timing reactions or experiments    c) Observing microscopic objects   d) Dispensing precise volumes of liquids 20. Which tool is used for filtering solids from liquids in the laboratory?     a) Beaker     b) Graduated cylinder     c) Funnel     d) Erlenmeyer flask a) Measuring temperature b) Filtering solutions c) Stirring and mixing liquids d) Measuring mass 21. Which laboratory equipment is used to protect the eyes from chemical splashes? a) Laboratory coat b) Safety goggles c) Gloves d) Face mask 22. Which instrument is used to separate two immiscible liquids, such as oil and water? a) Beaker b) Measuring cylinder c) Separating funnel d) Test tube 🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤 ⭐️Our Channel ⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/dam76 👆👆👆👆
Nov 23, 04:47 PM
15.7K
⭐️በትምህርት ስኬታማ ለመሆን ጠንክሮ ማጥናት ብቻ በቂ አይደለም - በብልሃት ማጥናት ነው። ✅ ጥረትን ወደ ውጤት የሚቀይሩ ውጤታማ የአጠናን ስልቶቹ የሚከተሉት ናቸው:- 🌟 1. ስታጠኑ ግልጽ የሆነ ዓላማ  ይኑራችሁ ✅የምታጠኑትን መጽሐፍ ወይም ደብተር እንዲሁ አትግለጡት- መጀመሪያ ለምን እንደምታጠኑ እወቁ። ✅እራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፡- በዚህ የጥናት ጊዜዬ ምን መረዳት ወይም ማሳካት እፈልጋለሁ? ✅በዓላማ የሚያጠና ተማሪ በትኩረት ያነባል፣ የተሻለ ያስታውሳል፣ ጊዜውን አያባክንም። ➡️ ምሳሌ፡- “ሳይንስ ወይም ባዮሎጂ አጠናለሁ” ከማለት ይልቅ “የሰው ልጅ ልብ እንዴት እንደሚሰራ ••• እረዳለሁ” በሉ። 🇪🇸 2. ተግባራዊ የንባብ ስልትን ተጠቀሙ፣ እንዲሁ ለማንበብ አትሞክሩ ✔️ማንበብ ብቻውን በቂ አይደለም። አእምሮ በንቃት ሲሳተፍ አንድን ነገር በተሻለ ሁኔታ መረዳት ትችላላችሁ። ለምሳሌ ይህንን ሞክሩ፦ ➡️ ያነበባችሁትን ነገር በራሳችሁ አገላለጽ ወይም ቃላት ከልሱት። ➡️ ፅንሰ-ሀሳቡን ለጓደኞቻችሁ አስረዱ። ➡️ በምታጠኑበት ጊዜ ለራሳችሁ ጥያቄዎችን ጠይቁ። 📌 አንድን ፅንሰ-ሀሳብ በቀላሉ ማስረዳት ከቻላችሁ፣ በትክክል ተረድታችሁታል ማለት ነው። ⏰ 3. ጊዜያችሁን በጥበብ አስተዳድሩ ✅ጊዜ ትልቁ ሀብት ነው። ስኬታማ ተማሪዎች ተነሳሽነትን አይጠብቁም - የራሳቸውን የጥናት መርሃ ግብር አዘጋጅተው በዚያ ይመራሉ። 📌 ጊዜያችሁን በጥበብ ለመጠቀም የሚከተሉትን ቴክኒኮች/ዘዴዎች ተጠቀሙ፦ ➡️ አእምሮአችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ ከ25–50 ደቂቃዎች ያህል በትኩረት አጥኑ። ➡️ በመካከል አጭር እረፍት ውሰዱ። ➡️ ከባድ ለሆኑ ትምህርቶች ቅድሚያ ስጡ #️⃣አስተውሉ: በየቀኑ የሚደረጉ ትናንሽ ነገር ግን ወጥ የሆኑ ጥረቶች በመጨረሻ ሰአት ላይ የሚኖር መጨናነቅን ይበልጣሉ። 🗓 4. አስቀድማችሁ በማቀድ በተደራጀ ሁኔታ አጥኑ 🔤ግልጽ የሆነ እቅድ ጭንቀትን ይቀንሳል፤ በራስ መተማመንንም ይጨምራል። ➡️ ማስታወሻ ደብተር ወይም እቅድ ማውጫ ተጠቀሙ። ➡️ ትላልቅ የጥናት ተግባራትን ወደ ትናንሽ ደረጃዎች ከፋፍሏቸው። ➡️ ዕለታዊ እና ሳምንታዊ የጥናት ግቦችን አዘጋጁ። 📌 ጊዜያችሁን ስታቅዱ፣ የወደፊት ሕይወታችሁን ትቆጣጠራላችሁ። 🔁 5. አዘውትራችሁ ከልሱ 🔤መርሳት ተፈጥሯዊ ነው—ነገር ግን ክለሳ መርሳትን ይፋለመዋል። ➡️ በጥናት ወቅት የምታዘጋጇቸውን ማስታወሻዎቻችሁን ምንጊዜም በ24 ሰዓታት ውስጥ ከልሱ። ➡️ ከዚህ በፊት የተጠኑ የተለያዩ ርዕሶችን በየሳምንቱ እንደገና ለማየት ሞክሩ። ➡️ ያለፉ ጥያቄዎችን በመስራት ተለማመዱ #️⃣አስተውሉ:  አንድን ነገር መደጋገም ችሎታን ይገነባል። ✅ 6. ማንበብ ብቻ ሳይሆን ለልምምድ ትኩረት ስጡ ✔️በተለይ እንደ ሂሳብ፣ ፊዚክስ ወይም ኬሚስትሪ ላሉ ትምህርቶች ልምምድ ሁሉም ነገር ነው። ➡️  ኘሮብሌሞችን ለመፍታት ጥረት አድርጉ Solve Problems ➡️ ማስታወሻዎችን (notes) ሳትመለከቱ እራሳችሁን ፈትሹ ➡️ ከስህተቶቻችሁ ተማሩ 📌 ስህተቶች ውድቀቶች አይደሉም—ምርጥ አስተማሪዎች ናቸው። ✔️ 7. ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግዱ አካባቢያችሁ ስኬታችሁን ይቀርፃል። ➡️ ስልካችሁን ከአጠገባችሁ አርቁ ወይም ድምፁን አጥፉት። ➡️ ጸጥ ያለ የጥናት ቦታ ምረጡ። ➡️ በአንዴ ብዙ ነገሮችን ከማከናወን ተቆጠቡ። 📌  ባለንበት ሃሳብን በሚከፋፍል ዓለም ውስጥ #ትኩረት ማድረግ ሃይልን የሚያጎናፅፍ ልማድ ነው። 💪 8. ሰውነታችሁን እና እምሮዎአችሁን ተንከባከቡ ✔️የደከመ አእምሮ ውጤታማ በሆነ መንገድ መማር አይችልም። ➡️ በቂ እንቅልፍ አግኙ ➡️ ጤናማ ምግብ ተመገቡ ➡️ በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ 📌 ጠንካራ ሰውነት ጠንካራ አእምሮን ይፈጥራል። 🚀 9. በየጊዜው አቅማችሁን ማሻሻል እንደምትችሉ እምነት ይኑራችሁ 👌ብዙ ተማሪዎች የሚወድቁት ከሌሎች ያነሰ የማሰብ ችሎታ ስላላቸው ሳይሆን በራሳቸው እምነት ስለሌላቸው ነው። አስታውሱ፡- 📌ብልህነት (የማሰብ/የመማር አቅም) በጥረት ያድጋል። 🌟 እያንዳንዱ ስኬታማ የሆነ ባለሙያ በአንድ ወቅት ጀማሪ ነበር። 🌟ያለፈው ውጤታችሁ የወደፊቱን አይገልጽም። 🌟 ለራሳችሁ እንዲህ በሉ፡- “ማንኛውንም ትምህርት መማር እችላለሁ። አሻሽላለሁ።” 🔣#ሸር 🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤 Our channel ⬇️⬇️⬇️⬇️ ❤️❤️❤️❤️ https://t.me/dam76
Nov 16, 11:49 AM
21.7K
✅የጤና ጉዳይ ✍️ለጤናችን ጽዋ እናንሳ !✍️ ⭐️ዕድሜህ 30ን ሲሻገር ለጤናህ መጠንቀቅ መጀመር አለብህ። 40ን ስትሻገር ግን የዘወትር ልማዶችህን ማስተካከል አለብህ።  አለዚያ ስኳር፣ ደም ግፊት ሌላም ሌላም ሊያስቸግሩህ ይችላሉ። ✅ሰውነትህ ምልክት ሲሰጥህ አዳምጠውና ተገቢውን ማስተካከያ አድርግ::ከምልክቱ በፊትም ይሁን በኋላ ለጥንቃቄ የሚከተሉትን ልማድ አድርግ። ✅፩) ከእንቅልፍ እንደተነቃህ ሁለት ብርጭቆ ውሃ ጠጣ። ✔️ውሃ የሰውነታችን ዋና ክፍል ነው። ውሃ ለጤናም ለውበትም ጠቃሚ ነው። ውሃ በበቂ መጠን ጠጣ። በቀን 8 ብርጭቆ ወይም 2 ሊትር ውሃ ጠጣ። ✔️ቢቻል በቫይታሚን የበለጸገ ውሃ ጠጣ። ይህንን የቫይታሚን ውሃ ካላገኘህ ሎሚ፣ ኩኩምበር፣ ዝንጅብል፣ እርድና ቀረፋ በመጠኑ ጨምረህ ጠጣ። ✅፪) ቁርስህን ቀለል ያለና በፕሮቲንና ገለባ/ፋይበር የበለጸገ ምግብ ብላ። ✔️ፕሮቲን ውድ ከመሰለህ እንቁላል፣ ለውዝ፣ አቮካዶ፣ ፉል አሉልህ። እናም ቁርስህን እንቁላል፣ ቆስጣ ወይም አቮካዶ ወይም ፉል ወይም ጩኮ ብላ። ✔️የሰሃንህ ግማሽ በጎመና ገመን ይሞላ። ቀሪው በፕሮቲን እና 10% ያህሉ በካርቦሃይድሬት ይሞላ። ዳቦ ስትበላ ገለባው በበዛ እና በጠቆረ ዱቄት የተሠራ ዳቦ ይሁን። ✅፫) ምሳህን ሲርብህ ብላ። ሳይርብህ ሰዓት ስለደረሰ ብቻ አትብላ። ✔️ምግብ ስትበላ ለጥጋብ ሩብ ጉዳይ ላይ አቁም። Hara hachi bu ይሉታል ጃፓኖች። ✅፬) ከምሽቱ 1:00 ሰዓት በኋላ ምግብ አትብላ። ✔️ የግድ አምሽተህ ከበላህም ምግብ ከበላህ በኋላ 3:00 ያህል ቆይተህ ተኛ። ✅፭) ቡና አታብዛ። በቀን 1 ወይም ቢበዛ 2 ስኒ በቀን በቂ ነው። ✔️ቢጫ ወይም ወርቃማ ቀለም ያለውን የዐረብ ዓይነት ቡና ጠጣ እንጂ ጥቁር ቡና አትጠጣ። ✅፮) በጎ በጎውን አስብ። 🌗 ከሰው ተጫወት። ሳቅ፣ ተዝናና። ጨፍጋጋ ሃሳቦች ላይ አትቆይ። ቂም አትያዝ። አምላክህን አመስግን። ጸልይ። ጸሎት የመንፈሳዊውን ዓለም የማይታየውን መዋጊያ መሳሪያ ነው። ✅፯) መጾምን አዘውትር። ብትችል በሳምንት 3 ቀን እስከ 9:00 ሰዓት ጹም። 🌖ብትችል ደግሞ ዘወትር በ4:00 ሰዓት እና 12:00 ሰዓት ብትበላ ጥሩ ነው። እኔ በ3:00 ሰዓት እና በ9:00 ሰዓት መብላት መርጣለሁ። ጾም ለውስጣዊ አካልህም ለአእምሮህም ጽዳት ወሳኝ ነገር ነው። ✅፰) በቂ እንቅልፍ ተኛ። 🌖ከምሽቱ 3:00 በኋላ ብትተኛ እና 11:00 ሰዓት መነሳትን ልማድ ብታደርግ ለጤናህ መልካም ነው። የእንቅልፍ ሰዓትህን አታዘበራርቅ። 🌘የእንቅልፍ እጥረት ያልታወቀበት የጤና ጸር ነው።ሲመሽ ከሞባይል ወደ መጽሓፍ ንባብ ዙር። ከ40 ዓመት በኋላ እንቅልፍህ የተመጠነ እና የተለመደ ይሁን። 🌘መስኮቱ አየር በማያስገባና በታፈነ ቤት ውስጥ አትተኛ። Sleep Apnea ስለሚባል ችግር አልሰማህም? Check! ✅፱) የጠዋት ፀሓይ ብትሞቅ ለጤናህ ይበጅሃል። የጠዋት ፀሓይ ለህጻን ልጅ ብቻ ነው ያለው ማን ነው? ✅፲) ተንቀሳቀስ። ✔️በእግርህ ፈጠን ፈጠን እያልክ ተራመድ፣ ደረጃ ውጣ። ጎንበስ ቀና በል። ስገድ። ተንጠራራ። ከቻልክ ደግሞ ጂም ገብተህ ዋኝ፣ ዱብ ዱብ በል፣ ብረት አንሳ። 😎🧑‍🩰🏃‍♀‍➡️🏃‍➡️ 💀💀💀💀 💀💀💀 via 👉amazing fact ቻናላችን ይህ ነው ⚡️⚡️⚡️⚡️ https://t.me/dam76
Nov 11, 04:29 AM
18.1K
⭐️3 ጊዜህ እንዳይባክን ማድረግ ያሉብህ ነገሮች ✅ጊዜህ ወደር የማይገኝለት ስጦታህ ነው። በተፈጥሮ ያገኘኸው ውድ የሆነ መዋለ-ንዋይህ ሆኗል። ሁላችንም ቀናችንን ከምንጀምርበት ስንቆጥር እኩል 24 ሰአታት አሉን። ነገር ግን ጥቂት ሰዎች እንዴት ልዩ እና ስኬታማ ይሆናሉ? ሌሎች ምንም ነገር እንዳልቻሉ በሚሰማቸው በእኩል ሰአት! 🌟🤲ቁልፉ ይሄው ነው በትክክል ጊዚያቸውን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ያውቁበታል! ⭐️እኒህን ሶስት ነገሮች ተመልከት። ጊዜህን በትክክል እንድትጠቀም ይረዱሃል። ✅1.አንደኛ 'የሁለት ደቂቃ ህግ' ✅ብዙ ጊዜ ላድርግ አላድርግ የማለት ማመንታቶች ጊዜህን ሳታውቀው ይሰርቁሃል። ምናልባት ለማድረrግ ብትወስን ያን ያህል ልትፈጽመው ከባድ አይሆንም። ስለዚህ አእምሮህን በሁለት ደቂቃ ውስጥ የማድረግ ውሳኔን እንዲችል አሰልጥነው። ✅2.ለትላልቅ አላማዎች ትናንሽ መነሳሻዎች ይኑሩህ 🌟ትላልቅ አላማዎችህ ያንተ መዳረሻ ምስል የምታስቀምጥባቸው ይሆናሉ። ትናንሽ መነሳሻዎችህ ደግሞ የምትሰራቸው ጥቃቅን ስራዎች ይሆናሉ። እነዚህም የህይወትህን ዋና ግብ እውን የምታደርግባቸው ብልሃትህ ይሆናሉ። ጥቃቅን ነገሮችን መስራት የቀን ተቀን ልማድህ ሊሆን ይገባል። አሊያ ትልቁን ማሳካት አይቻልም። ✅3. በይበልጥ አንድ ስራ ላይ አተኩር። 🌟ብዙ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ ሃይል ማጥፋት ውጤታማ አያደርግም። ጊዜን በመባከን ማጥፋት ይሆናል። ሳይኮሎጂ መኪና እየነዱ ቴክስት መጻጻፍ  አደጋ እንደሚኖረው ያስረዳል። ⭐️ ሰው ሁለት ወይም ሶስት ነገሮች ላይ እኩል ትኩረት ማድረግ ስለማይችል ነው። አንዱ ላይ ካተኮርክ ግን ውጤታማ እንደሚያደርግህ አያጠራጥርም። ስለዚህ ትኩረትህን አላማህ ላይ አድርግ። ያኔ በጥራት፣ በከፍታ የምትፈልገውን ታሳካለህ። ✅መልካም ቀን via 👌በልኬት_ወደ_ስኬት መጽሀፍ 🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤 🫴🫴🫴🫴 https://t.me/dam76
Nov 7, 10:34 AM
20.4K

Safety & Compliance Disclaimer

TelePilot Pro is not affiliated with Telegram. Listings are based on publicly available community information. We index public groups, channels, and bots only. No private user data, phone numbers, or locked session files are stored or displayed.

TelePilot Pro Automation

Scale Your Telegram Community Faster

Join thousands of marketers using TelePilot Pro to bulk message, scrape targeted members, and manage groups on autopilot. Outperform competitors with our 40+ professional automation tools.